Cholera

ኢትዮጵያ: በሶማሌ ክልል ጉራዳሞሌ ለተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ኤም ኤስ ኤፍ ያደረገው ድጋፍ

በቅድመ ምላሽ እና የመከላከያ እርምጃዎች ኮሌራን መቆጣጠር

በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ የኤምኤስኤፍ ቡድን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሊበን ዞን በጉራዳሞሌ ወረዳ ለተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ለአንድ ወር ያህል ምላሽ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ተጉዟል።

ኤም ኤስ ኤፍ በፍጥነት የኮሌራ ህክምና ማዕከል አቋቁሞ በኮሌራ ከተጠቁ አካባቢዎች አንዱ በሆነው እና የጤና አጠባበቅ ውስንነት ላላቸው ወደ 75,000 ይአህል ተፈናቃዮች በሚገኙበት በአደሌይ ካምብ ለሚገኙ ህሙማን የህክምና ድጋፍ አድርጓል፡፡

 

ንጹህ የመጠጥ ውሃ የለም

የኤምኤስኤፍ ፕሮጀክት አስተባባሪ አና ባይለንድ “ይህ ካምፕ በጣም ጥቂት መጸዳጃ ቤቶች ያሉት እና በቂ መጠለያ ያልነበረው ሲሆን ብዙ ሰዎች በየቀኑ ይመጡ ወደዝያው ነበር። በዚያን ጊዜ በአዴሌ የሚገኘው ማህበረሰብ ምንም አይነት የመጠጥ ውሃ ባለማግኘቱ በቀላሉ ሊበከል በሚችለው የወራጅ ወንዝን እንደ መጠጥ ውሃ ምንጭ አድርጎ ይጠቀም ነበር፡፡

“ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆነ እዝያ ተጠልለው የሚገኙት ተፈናቃዮች እንደነገሩን ከሆነ የኮሌራ ወረርሽኝ የበለጠ ይዛመታል የሚል ስጋት ነበራቸው። ብዙዎች እ.ኤ.አ በ2017 በሊባን ዞን ስላጋጠመው ትልቅ ወረርሽኝ በማሰብ ያ ሁኔታ እንደገና ሊከሰት ይችላል ብለው ይሰጋሉ" ትላለች አና።

ቡድኑ ህብረተሰቡ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እንዲያገኝ ለማድረግ የእጅ መታጠቢያ ስፍራዎችን በመትከል 12 መጸዳጃ ቤቶችን እና በአቅራቢያው ካለ ወንዝ አጠገብ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ገንብተዋል።

in_guradamole_the_team_installed_water_distribution_points.jpeg

የቤት ውስጥ ርጭት

የውሃ እና የአካባቢ ጽዳትና ንፅህና ቡድን በተቻለ ፍጥነት ለመጨረስ ባትሪዎችን በመጠቀም እስከ ምሽት ድረስ በጣም ጠንክሮ ሰርቷል። ሾፌሮችን ጨምሮ ሁሉም ሰው ዕቃውን ወደ ወንዙ በማውረድ ወይም የተለያዩ ቱቦዎችን እና ክፍሎችን በመገጣጠም የእርዳታ እጁን ዘርግቷል” ትላለች አና።

“የእኛ የጤና ማስተዋወቅ ቡድኖቻችን የመድሀኒት ርጭትን አስፈላጊነት በሚገባ ካብራሩ በኋላ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ቀና ትብብራቸውን መስጠት ጀመሩ፡፡ የእኛን ወደ አካባቢው መምጣት ሲመለከቱም ርቀው ባሉበት በመምጣት ቤታቸውን በመድሀኒት እንድንረጭ ይጠይቁን ነበር፡፡ የቀጠርናቸው አራት የቀን ሰራተኞች ሰብላቸውን ለመርጨት የሚጠቀሙበት መሳሪያ በመሆኑ በትክክል እንዴት እንደሚጠቀሙ የሚያውቁ ገበሬዎች ነበሩ” ትላለች አና።

kersa_dula_latrine_contruction.jpg

"የእሷ የልብ ምት ምን ያህል እንደሚሰማኝ አሳየሁት።"

በህክምና ክፍሉ ውስጥ የሕክምና ባልደረቦች ለኮሌራ ህሙማን የውሃ ማጠጣትን እና ለከባድ ህመሞች በፀረ-ባክቴሪያ ህክምና ሰጥተው ነበር። በቡድኑ ውስጥ ካሉት ሁለቱ የኤምኤስኤፍ ነርሶች አንዷ ዴኒዝ ፖቭኒን “ከልጆቻቸው ጋር በዚህ ላይ ተሳታፊ በነበሩት አባቶች ቁጥር በጣም አስደንቆኛል” ብላለች። “ከአነዚህም መካከል አንድ ሴት ልጁ የኮሌራ ሕክምና ክፍል የደረሰች በጣም ከባድ በሆነ ሁኔታ የደም ሥር ፈሳሽ ያስፈልጋት የነበረ አባት በእጅጉ ጎልቶ ታይቷል። በመጀመሪያው ሰአት የልቧን ምት እንቅስቃሴ ለመከታተል በተደጋጋሚ ወደ ተኛችበት ክፍል መጣሁ። የልጅቷ አባት የእኔን የጣት እንስቃሴ ምልክቶች እየተከታተለ በመኮረጅ ላይ መሆኑንም አስተዋልኩ። “ቃላቶችን ሳልጠቀም፣ የልጁ የልብ ምት እንዴት እንደሚሰማኝ አሳየሁት፡ እሱም ልክ እንደዚሁ አደረገ እና በእጆቹ የልብ

ምቱን እንቅስቃሴ በፈገግታ እያሳየ እሱም የልብ ምቱ እየተሰማው እንደሆነ አሳየኝ፡፡ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ወደ መኝታ ክፍሉ በሄድኩ ቁጥር ይህ በፈገግታ የተሞላ አባት ከልጁ አልጋ አጠገብ ሆኖ ምቾት እየተሰማት መሆኗን እና ንፁህ መሆኗን ያረጋግጣል፡፡ በእያንዳንዱም ቀን ልጁ እየተሻላት እና እየበረታች ነበር። በሶስተኛው ቀን ልጅቱ ህክምናዋን ጨርሳ ከክፍሉ በመውጣት ላይ ሳለች እኔ በመኝታ ክፍሉ እየተዟዟርኩ ክትትል እያደረግሁ ነበር። አባትየው እንደ ልዕልት ሮዝ ቀለም ያለው ልብስ ለብሶ በደስታ እያንጸባረቀ ከልጁ አጠገብ ቆሞ ነበር” ትላለች ዴኒዝ።

 

ኤም ኤስ ኤፍ በቀርሳ ዱላ ለሁለተኛ ጊዜ የኮሌራ ወረርሽኝ ምላሽ ይሰጣል

በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ኤምኤስኤፍ በሊባን ዞን በቀርሳ ዱላ ለተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ አሥር አልጋ ያለው የኮሌራ ሕክምና ክፍል ከመጸዳጃ ቤትና ከሻወር ጋር በሌላ ድርጅት የተበረከተ መሣሪያ የድጋፍ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ቡድኑ ለህክምና ባለሙያዎች በሽታ ትርጓሜ (የኬዝ ፍቺ) እና የጉዳይ አስተዳደር ስልጠና በማዘጋጀት ኢንፌክሽኑን በመቆጣጠር እና በመከላከል እንዲሁም የኮሌራ ህሙማን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል። ሌላ የማረጋጊያ ክፍል በባሊያት ከመጸዳጃ ቤት እና ከመታጠቢያ ገንዳ ጋር በፍጥነት ተገንብቷል።

msf_cholera_intervention_in_guradamole_provided_access_to_clean_safe_drinking_water.jpg

የህክምና ድጋፎች (ምላሽ) እና መከላከል ዕቅዶች

የኮሌራ ወረርሽኝ ምላሽ እና የመከላከያ እቅዶች እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው፡፡ ቡድኑ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ንፅህናን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ከክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ጋር በመሆን በኮሌራ ጉዳይ አያያዝና ኢንፌክሽን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ለአካባቢው የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።

በአጠቃላይ በጉራዳሞሌ 155 ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን በሚያሳዝን ሁኔታ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል። በቀርሳ ዱላ ደግሞ 44 የኮሌራ ተጠቂዎች እና 2 ሞት ተመዝግቧል። ቡድኖቻችን ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን መሬት ላይ ያከናወናቸው ስራዎች የበርካቶችን ህይወት መታደግ ችለዋል።

የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር በፍጥነት የቀነሰ ሲሆን በጉራዳሞሌ እና ቀርሱ ዱላ ያደረግነው ድጋፍና እገዛ በኋላ አንድም የኮሌራ ታማሚ አልተመዘገበም። ይሁን እንጂ ይህ መልካም ዜና ቢሆንም ቡድኖቹ ነቅተው በመጠበቅ ሁኔታውን እየተከታተሉ ሲሆን አዳዲስ ወረርሽኞች ሲከሰቱ ጣልቃ ለመግባት እና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው።