MSF/Mohamed Adan
Epidemics

በአለም አቀፍ ደረጃ ለተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ክትባት እጥረት መፍትሄ ሊሆን የሚችል የወረርሽኝ ምላሽ

እ.ኤ.አ. በ2023/24 ኢትዮጵያን ጨምሮ በ16 ሀገራት የኮሌራ ወረርሽኝ በሀገራቸው መከሰቱን አውጀዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሌራ ክትባት እጥረት እንዲሁም ባለፉት ሁለት አመታት ወዲህ በአራት እጥፍ ያደገውን የኮሌራ ክትባት ፍላጎትን ተከትሎ ሀገራት የወረርሽሽኝ ምላሽ አሰጣጥ መንገዳቸውን ማዘመን ይጠበቅባቸዋል።

ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (ኤም.ኤስ.ኤፍ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማ ለተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል እና በሽታው (ወረርሺኙ) የተከሰተበትን አካባቢ ትኩረት ያደረገ የምላሽ የመስጠት ዘዴ (Case Area Targeted Intervention (CATI) ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሺኝ ከጥቅምት ወር ጀምሮ በወረርሺኝ ደረጃ የታወጀ ሲሆን ፤ ወረርሺኙ ጂግጂጋን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ ከፍሎች ትከስቷል።

ካቲ (CATI) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ

“የኮሌራ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ በበሽታው ከተያዘው ሰው ቤት በ200 ሜትር ርቀት ዙሪያ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በበሽታው የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ለዚህም ነው በሶማሌ ክልል ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ካቲን (CATI) ተግባራዊ እያደረግን ያለነው” ዳንኤል ጉዲና ፣ የኤም.ኤስ.ኤፍ ኤፒዲሚዮሎጂስት።

ኤም.ኤስ.ኤፍ በኮሌራ የተያዙ ሰዎችን ዝርዝር ከክልሉ ጤና ቢሮ በየቀኑ የሚቀበል ሲሆን፤ አያንዳንዱ ታማሚ የሚኖርበትን ስፍራ ከተየ በኋላ፣ ቡድኑ የታማሚው መኖሪያን ጨምሮ በዙሪያው ላሉ አስር ተጨማሪ አባወራዎች ፀረ ተባይ መድሃኒት ይረጫል። በእነዚህ አስር ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የኮሌራ ክትባት እና ጽረ-ባክቴሪያ እንዲውስዱ ይደረጋል፤ በተጨማሪም እንደ ጀሪካን ፣ የውሃ ባልዲ ፣ ሳሙና እና የውሃ ማከሚያ ኬሚካሎችን ያካተተ የንፅህና መጠበቂያ ኪት ይሰጣቸዋል።

ካቲ (CATI) ከተለመድው የኮሌራ ወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥ ወይም ሰፊ የሆነ መልክዓ ምድራዊ አካባቢ ላይ ብዙ ህብረተሰብን በአንድ ጊዜ ለመድረስ ከሚተግበረው እና ከፍተኛ ግብዓት ከሚፈልገው ምላሽ አሰጣጥ የተለየ ነው፣

የሶማሌ ክልል ከሶማሊያ፣ ከጅቡቲ እና ከኬንያ የሚዋሰን እና በኢትዮጵያ ሁለተኛው ትልቁ ክልል በመሆኑ ሰፊ እና ከፍተኛ ግብዓት የሚጠይቅ የወረርሺኝ ምላሽ ከመተግበር ይልቅ፣ እንደ ካቲ (CATI) ያለ ወረርሺኙ የተክሰተበትን ቦታ ማእከል በማድረግ የሚሰጥ የወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥ ዘዴ ተመራጭ ነው። ካቲ (CATI) የኮሌራ በሽታ እንዳይስፋፋ በበሽታው የተያዘ ሰው ከተገኘብት ጊዜ አንስቶ በንቃት ይተገበራል። ይህ ዘዴ በኢትዮጵያ ሲተገበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

Members of MSF CATI team walking from house to house to respond to the cholera outbreak in Jigjiga, Ethiopia
Members of MSF CATI team walking from house to house to respond to the cholera outbreak in Jigjiga, Ethiopia
MSF/Mohamed Adan

ኤም.ኤስ.ኤፍ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከሚሰራው በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ወደ ህክምና እንዲመጡ ከማደረግ እና የመከላከያ መንገዶችን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ በጽኑ ለታመሙ ታካሚዎች አጠቃላይ ህክምና እና እንክብካቤ ለመስጠት እንዲያስችል በአየርደጋ ጤና ጣቢያ የኮሌራ ህክምና ማዕከል (CTC) እንዲቋቋም ድጋፍ አድርጓል።

በተጨማሪም በጅግጅጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የኮሌራ ህክምና ዩኒት (CTU) እንዲሁም በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች አምስት የበሽታው ምልክት የታየባቸውን ሰዎች ለመርዳት የተቋቋሙ ማእከላትን (ORP) ገንብቷል።

ሁሉም የካቲ (CATI) ቡድኖች ከኤም.ኤስ.ኤፍ እና ከክልሉ ጤና ቢሮ በተወጣጡ ባለሙያዎች የተምሰረቱ ናቸው። ቡድኖቹ የበሽታ ቅኝት እና መረጃ የሚሰበስቡ፣ ክትባቶችን የሚሰጡ ነርሶችን፣ የውሃ የአካባቢ ጽዳትና ንፅህና

ተቆጣጣሪዎች፣ የጤና አጠባበቅ አስተማሪዎችን እና ኢንፌክሽን መከላከል እና መቆጣጠር ባለሙያዎችን ያካተቱ ሲሆን፤ በተጨማሪም የአካባቢው አስተዳደር ወይም የቀበሌ ተወካይ ከቡድኑ ጋር በመሆን ሂደቱን ያስተባብራሉ።

የካቲ (CATI) ተስፋ ሰጪ ውጤቶች

“በክትባት እጥረት ሳቢያ ሰፊ የክትባት ዘመቻዎችን መስጠትን ጨምሮ ወረርሽኙን ለመዋጋት አቅማችን ውስን በመሆኑ፣ የካቲ መተግበር ክልሉ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመግታት ለሚያደርገው ርብርብ ተስፋ ሰጪ ነው’’ ኤርሚያስ አማረ፣ በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ደንገተኛ ወረርሽኝ ምላሽ ባለሙያ (መኮንን) እና የካቲ (CATI) አስተባባሪ።

እ.ኤ.አ. ከህዳር 2023 እስከ የካቲት 2024 ኤም.ኤስ.ኤፍ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከ800 በላይ የኮሌራ ታማሚዎችን ማከም ሲችል፣ ከ8,000 ለሚበልጡ ሰዎች የኮሌራ ክትባቶች፣ 1,700 ለሚሆኑ ቤተሰቦች የንፅህና መጠበቂያ ኪቶችን እና የጤና አጠባበቅ ትምህርቶችን ሰጥቷል።

ምንም እንኳን የካቲ (CATI) አተገባበር በኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም በሙከራ ደረጃ ላይ ያለ እና የወረርሺኙን ጉዳት ከመቀነስ አንጻር ያመጣው ውጤት ተጨማሪ ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆንም የታዩት ጅማሪ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ ናቸው።

A member of the CATI team administers an oral cholera vaccine to a child in Jigjiga, Ethiopia
A member of the CATI team administers an oral cholera vaccine to a child in Jigjiga, Ethiopia
MSF/Mohamed Adan

ኮሌራ በሰአታት ውስጥ ሊገድል ይችላል ነገር ግን መከላከል እና መታከም የሚችል ነው

በአለም አቀፍ ደረጃ እስከ ጥር ወር ድረስ 735,000 የኮሌራ ተጠቂዎች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን ይህም እ.ኤ.አ. በ2022 ከተመዘገቡት ሰዎች ቁጥር 40 በመቶ ጨምሯል።

በጥር ውር ብቻ በአለም አቀፍ ደረጃ 41,000 የሚጠጉ ሰዎች በኮሌራ በሽታ የተያዙ ሲሆን 775 ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተይዘው ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። በኢትዮጵያም እ.ኤ.አ. ከነሃሴ 2022 እስከ የካቲት 2024 ድረስ በድምሩ 36,061 ሰዎች በኮሌራ የተያዙ ሲሆን 515 ሰዎች ሞተዋል። ከጥር 1 እስከ የካቲት 26, 2024 ብቻ 4,870 ሰዎች በበሽታው ተጠቅተዋል። ሶማሌ ክልልም በኮሌራ ወረርሺኝ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት፣ እስከ መጋቢት አጋማሽ ድረስ የሚመረተው የኮሌራ ክትባት በሙሉ ወረርሺኙ ለተከሰተባቸው ሀገራት የተመደበ በመሆኑ አሁን በዓለም ላይ ያለው የኮሌራ ክትባት ክምችት ባዶ ነው። ነገር ግን የክትባቱ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

ኤም.ኤስ.ኤፍ ይህ የአቅርቦት እጥረት የሚያስከትለውን አስከፊ መዘዝ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳሰቢያ በመስጠት አምራቾች የክትባቱን ምርት መጠን በአፋጣኝ እንዲጨምሩ እንዲሁም ለአዳዲስ አምራቾች ተጨማሪ ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ የቁጥጥር ሂደቶችን በማፋጠን የምርት መጠን መጨመር እንዲቻል ሲጠይቅ ቆይቷል።

የክትባት አቅርቦቱ፤ እየጨመረ የመጣውን በወረርሽኙ የሚጠቁ ሰዎችን ለማከም ከሚያስፈልገው በታች ቢሆንም፣ የካቲ (CATI) ትግበራ የዚህን ተጽእኖ ለመቀነስ ከሚጠቅሙ የወረርሺኝ ምላሽ መስጫ ዝዴዎች ውስጥ አንዱ ነው።

ኤም.ኤስ.ኤፍ በሌሎች የኮሌራ ወረርሺኝ በተከሰተባቸው እንደ ሄይቲ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባሉ አገሮች ካቲን (CATI)በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ጉዳት መቀነስ ችሏል።

ኤም.ኤስ.ኤፍ ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ይህ የወረርሺኝ ምላሽ አሰጣጥ ዘዴ በጅግጅጋ ከተማ ያመጣውን ውጤት በማጥናት ላይ ይገኛል፣ ውጤቱን በማየትም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ለመተግበር በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከጅግጅጋ ከተማ በተጨማሪም ኤም.ኤስ.ኤፍ በሶማሌ ክልል ሌላኛው ትልቅ ከተማ በሆነችው ቀብሪደሃር ከተማ የኮሌራ ወረርሺኝ መከሰቱን ተከትሎ የወረርሺኝ ምላሽ በመስጠት ላይ ይግኛል።

በተጨማሪም ኤም.ኤስ.ኤፍ በካቲ (CATI) አተገባበር ላይ ከጅግጅጋ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በላፋሲሴ ከተማ ለኮሌራ ወረርሺኝ ምላሽ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የክልሉ ጤና ቢሮ ባለሞያዎች ስልጠናዎችን ሰጥቷል።

እ.ኤ.አ. በ1961 የጀመረውና እስካሁን ባላቆመው ዓለም አቀፍ የኮሌራ ወረርሽኝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሙሉ በሙሉ መከላከል በሚቻልው በሽታ ምክንያት ለሞት ተዳርገዋል።

በክትባት አምራቾች ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ምክንያት የኮሌራ ወረርሺኝ የሚያደርሰውን ጉዳት በካቲ (CATI)እንዴት መቀንስ እንደሚቻል ለሌሎች ሀገራት ለማሳየት ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና መጫወት ትችላለች።

እ.ኤ.አ. ሰኔ 2021 ባልደረቦቻችን ማሪያ ሄርናንዴዝ ማታስ፣ ቴዎድሮስ ገብረማርያም ገብረሚካኤል እና ዮሃንስ ሃለፎም ረዳ በግብረሰናይ ሰራተኞች መሆናቸው በግልፅ እየታወቀ በትግራይ ክልል በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ሰፊ ውይይት ብናደርግም በእለቱ በባልደረባዎቻችን ላይ ስለደረሰው ነገር ምንም አይነት ተዓማኒነት ያለው ምላሽ አላገኘንም። ኤምኤስኤፍ ለሞታቸው ተጠያቂነትን ለማስፈን ሁሉንም አማራጮች መጠቀሙን ይቀጥላል። ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ የግብረሰናይ ድርጅት ሰራተኞችን ደህንነት ለማሻሻል አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ተስፋ እናደርጋለን።

Up Next
Attacks on medical care
Article 24 June 2024