ዛሬ፣ መጋቢት ፩፯ ቀን፣ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ በትግራይ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ባልደረቦቻችን ማሪያ ሄርናንዴዝ፣ ቴዎድሮስ ገብረማርያም እና ዮሃንስ ሃለፎም በሰኔ 24 ቀን 2013 የተገደሉበትን ሁናቴ የሚገልጽ የምርመራ ዘገባ አቅርቧል። ይሄው ዘገባ ለግድያው ተጠያቂው በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሀይል ሲሆን በተለይም አንድ የመከላከያ ኮማንደር ቀጥተኛ ተሳትፎ የተፈጸመ ነው ሲል በይፋ አትቷል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዲሪ) መንግስት በዚህ ሆን ተብሎ በባልደረቦቻችን ላይ ለተፈጸመ ግድያ ዙሪያ በቀረበው የኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ግልጽ ምላሽ እንዲሰጠን አንጠይቃለን፡፡
ከባልደረቦቻችን አሰቃቂ ሞት ጀምሮ፣ MSF ከእነዚህ ግድያዎች በስተጀርባ ያለውን ሁኔታ ለመረዳት እና የኃላፊነት እውቅና ለማግኘት ያለ እረፍት ሲጥር ቆይቷል፡፡ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ያጋራነውና የድርጅታችን የውስጥ ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶች ወንጀለኞቹ እነማን እንደሆኑ እና አላማቸውን በእርግጠኝነት አላረጋገጡልንም።
በአደባባይም ሆነ በሁለት ወገን ግድያው በተፈፀመበት አካባቢ ያሉትን ሁለቱን ወገኖች ማለትም የሀገር መከላከያ ሀይል እና ህወሓትን በማሳተፍ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበናል። የእነርሱን የምርመራ ውጤት እና ግምገማ ከእኛ እና ከማሪያ፣ ቴድሮስ እና የዮሐንስ ቤተሰቦች ጋር እንዲያካፍሉ ጠይቀናል። እስከዛሬ ድረስ ለግድያው መንስኤ የሆኑት ሁኔታዎች ወይም ለኃላፊነት እውቅና ስለሰጡን ሁኔታዎች ምንም ግልጽነት ያለው ምላሽ አልሰጡንም፡፡
በዚያ አስከፊ ቀን ስለተፈጠረው ነገር ከሁሉም አካላት ግልጽነት እንፈልጋለን፡፡ በመሆኑም ይህንኑ መረጃ ለማግኘት የሁለትዮሽ ተሳትፎአችንን እንቀጥላለን።
በመላው ኢትዮጵያ የህክምና እርዳታ እና እርዳታ የሚሰጡ የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ደህንነት እንደዚህ አይነት አሳዛኝ ክስተት ዳግም እንዳይከሰት በቂ እርምጃ እንዲወሰድ በአስቸኳይ እንጠይቃለን። የማሪያ፣ የቴድሮስ እና የዮሐንስ ትዝታ፣ የቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና ባልደረቦቻቸው ስቃይ መፅናናትን እና ጉዳያቸው እንዲቋጭ ይፈልጋሉ። እኛም ለዚህ ጉዳይ አስቸኳይ ምላሽ እንሻለን።
Read in English